የተጀመረዉ የአዉሮፓ ኮንሰርት በሄልስንኪ ከተማ ተጠናቋአል

last-eurpe

ቅዳሜ ታህሳስ 11 የተጀመረዉ የአዉሮፓ ኮንሰርት ስድስት አገራትን ዞሮ ትላንትና በሄልስንኪ ከተማ በግሎሪያ ክለብ በሰላም ተጠናቋአል።……ይህ ኮንሰርት ጅማሬዉ ላይ መሰናክሎች የነበሩበት ነዉና የችግሩ ፍንጥቅጣቂ ሁሉንም አገሮች ነካክቶ ስለነበረ….በየከተማዉ የነበሩት ፕሮሞተሮች እና እስፖንሰሮች ችግሩን በህብረት ስለተወጡት ኮንሰርቱ ሰላማዊ፤ ቀለማዊ ፍቅራዊ እይታ እንዲኖረዉ አድርገዉታል።…..በዚህ በአዉሮፓ ኮንሰርት ካጠገባችን ለነበራችሁ አፍቃሪዎቻችን እና የኮንሰርታችን ታዳሚዎች በተጨማሪ  ይህ ስራ እንዲሳካ በግናባር ላይ ሆነዉ ትልቁን መሰዋትነት ለተወጡት

1፡ ለኦስሎ ፕሮሞተሮች
2፡ ስዊድን ላለዉ የሰላም ድርጅት
3፡ የፍራንክፈርት ሸገር ካፌ
4፡ ስዊዘርላነድ ላሉት አሪፍ ኢንተርቴመንት እና ጅኔቫ ላሉት የአዲስ አበባ ሬስቶራንት
5፡ ለአምስተርዳሙ ሻሎም ኢንተርቴመንት
6፡ እንዲሁም ኮንሰርቱን ላሳረገልን ሄልስንኪ ኢትዮ ማርኬት ቶማስ እና ቤተሰቡን ስናመሰግን ከታላቅ አክብሮት እና ክብርም ጭምር ጋራ ነዉ…እጅ ነስተናል።…..በዚህ በአዉሮፓ ኮንሰርት ከህጳናት ጋራ እንድንገናኘ በስዊድን፤ ስዊዘርላንድ እና አምስተርዳም ለተባበራችሁን ወድሞች እና እህቶቻችን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነዉ።….ወደ አዉሮፓም ስንመጣ ሆነ አዉሮፓም ሆነን ጉዟችን ቀና እንዲሆን ላደረገዉ ጀርመን ያለዉን አቢሲንያ ትራቨልን ስናመሰግን ከልብ ነዉ….ይህ የፍቅር እና የሰላም የኮንሰርት ጉዞ ለተወሰነ ጊዜ እረፍት ያደርግ እና ጉዞዉን ይቀጥላል።

ሰላም ላገራችን
ፍቅር እና ጤና ለህዝባችን
ፍቅር ያሸንፋል
ጉዞዉ ይቀጥላል።One Response

  1. keflom says:

    ይፍቅር አባሳደር መልካም እርፍት ይሁንልህ። እግዚአቢሄር ካንተ ጋር ይሁን። አሜን

Leave a Reply to keflom