Artist Hachalu Hundessa Shot Dead

Hachalu Hundessa

A Young Outspoken Artist Hachalu Hundessa Shot Dead on Monday evening.

Artist Haacaaluu Hundeessaa, the prominent Oromo singer, songwriter, was shot dead today in Ethiopia’s capital Addis Abeba around Galan Condominium site. He was admitted to Tirunesh Beijing General Hospital but died of his injuries shortly after. R.I.P!

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው ጣሰው የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን አሟሟት በተመለከተ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አመሻሹ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። ኮሚሽነሩ በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመኪናው ወርዶ እንደተመለሰና ፤ ወደ መኪናው ከገባ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ የመኪናውን በር ከፍተው በጥይት መትተውታል ብለዋል። ድምፃዊው ከመኪናው ለምን ወርዶ እንደተመለሰ ኮሚሽነሩ ያሉት ነገር የለም።

ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው በወንጀል ድርጊቱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች መኖራቸውን አስታውሰው “በክትትል ሥር ያሉም አሉ” ብለዋል።

የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በጋራ ማዋቀራቸውን የገለፁት ኮሚሽነሩ ቀን ከማታ መረጃዎች ሳይጠፉ ከወንጀል ሥፍራ አስፈላጊ መረጃዎችን ለመውሰድ እየሰሩ መሆናውን ገልፀዋል።

አክለውም “ከእሱ ጋር የተያያዙ ኬዞችን በማጣራት በአጭር ጊዜ ለህብረተሰቡ የበሰለ መረጃ እናቀርባለን ብለን እናምናለን” ብለዋል ኮሚሽነር ጄነራሉ።

“የወንጀሉ አፈጻጸም የተደራጀ እና የረቀቀ ስለሆነ ትዕግስት የሚጠይቅ ነው” ያሉት ኮሚሽነር ጄነራሉ፤ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች ላይ ግድያ ከሚፈጸምባቸው ምክያቶች አንዱ “አገር ወደ ትርምስ እንድትገባ ነው” ብለዋል።

“ስለዚህ ይህን የምርመራ አካላችን አድርገን በጥንቃቄ ጠንካራ መርማሪዎች መድበን የማጣራት ሥራው በስፋት እየተሰራ ነው የሚገኘው” በማለት አስረድተዋል።

ኮሚሽነሩ “በድርጊቱ የተቆጡ ወጣቶች የሰላማዊ ዜጎች ንብረትን በአዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በተለያየ የአገራችን ክፍሎች እንዳወደሙ መረጃ ደርሶናል” በማለት መሰል ድርጊቶች ስህተት መሆናቸውን ጠቁመው “እያንዳንዱ እርምጃችን ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ መሆን አለበት” በማለት መልዕክት አስተላለፈዋል።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.